ኪፕ ኩል ዲሲ

የኮሎምቢያ ዲስትሪክት በጣም ከፍተኛ ሙቀት መቋቋሚያ ስልት

 

 

የሙቀት መጠን እንደሚጨምር በሚተነበይበት ጊዜ እና የሙቀት ሞገድ የበለጠ ደጋግሞ እና በከባድ ሁኔታ እንደሚከሰት በሚጠበቅበት ባሁኑ ወቅት፣ የኮሎምቢያ ዲስትሪክት የሙቀት መጠንን የሚጨምሩ ነገሮችን ለመቀነስ መስራት መቀጠሉ ወሳኝ ነው፣ ኗሪዎችን እየጠበቀ እና የማህበረሰብ የመቋቋም ችሎታን እየገነባ።

ይህ ተነሳሽነት በከንቲባ ሙሪዬል ባውሰር አመራር ስር የተሰሩ በርካታ የዲስትሪክት እቅዶች፣ የሚከተሉትን ጨምሮ፣ ላይ ይገነባል፥

 ክላይሜት ሬዲ ዲሲ (Climate Ready DC)  የዲስትሪክቱ የአየር ሁኔታ መቋቋሚያ ነው እና ዲስትሪክቱ ለአየር ሁኔታ ለውጥ አጠቃላይ ተጽዕኖ የሚዘጋጅባቸው መንገዶችን ያስቀምጣል።

 ሬዚሌንት ዲሲ (Resilient DC)  የዲስትሪክቱ አጠቃላይ የመቋቋም ችሎታ ስትራቴጂ ነው እና ዲስትሪክቱ በርካታ የተለያዩ ዓይነት ሥር የሰደዱ ጭንቀቶች እና አጣዳፊ ድንጋጤዎች በሚኖሩበት ጊዜ የሚያልፍባቸው፣ የሚቋቋምባቸው፣ እና የሚያድግባቸው መንገዶችን ያስቀምጣል።

 ንጹህ ኋይል (Clean Energy DC)  ዲስትሪክቱ በ2032 የአረንጓዴ ቤት የጋዝ ልቀቶችን በ 50% ቅናሽ ለማሳካት የያዘ እቅድ ነው።

 የነጻ ካርቦን ዲሲ (Carbon Free DC)  ዲስትሪክቱ በ2050 የካርቦን ምጣኔነትን ለማሳካት ያዘጋጀ ስትራቴጂ ነው።

 ሰስቴይነብል ዲሲ (Sustainable DC 2.0)  ዲስትሪክቱን በጣም ጤናማ፣ በጣም አረንጓዴ፣ ለሁሉም ኗሪዎች ከሁሉም በላይ ለመኖር ምቹ የሆነች ከተማ ለማድረግ ዲስትሪክቱ የያዘው አጠቃላይ እቅድ ነው።

 ሙቀት ድንገተኛ ሁኔታ እቅድ የሙቀት መጠን ወይም የሙቀት ኢንዴክስ 95° F ሲደርስ ኗሪዎች የሚያርፉባቸው የማቀዝቀዣ ማእከላትን ለማስጀመር ዲስትሪክቱ የያዘ እቅድ ነው።

ይህ ስትራቴጂ፣ Keep Cool DC፣ ከተማውን ለማቀዝቀዝ እና ኗሪዎች ደህና ሆነው እንዲቆዩ መቀጠል የምንችልባቸው መንገዶች ላይ ትኩረት በማድረግ በዲስትሪክት መንግስት ውስጥ እነዚህን እየተካሄዱ ያሉ ጥረቶችን ይደግፋል።


የህብረተሰብ ድምጾች

የበለጠ ሞቃታማ የሆነ የወደፊት ጊዜ ትንበያዎች ከግምት ውስጥ ሳይገቡ፣ የዲስትሪክት ኗሪዎች ዛሬ ላይ ቀድሞውኑ ሙቀትን ተቋቋመዋል። የዚህ ስትራቴጂ ዝግጅት ወቅት፣ DOEE የዲስትሪክት ኗሪዎች በጣም ከባድ ሙቀት የተመለከተ ስላላቸው እንዲማሩ እና ሙቀትን ለመቀነስ የተለያዩ መንገዶች ላይ እንዲወያዩ አሳትፏቸዋል። DOEE ከዲስትሪክት ኗሪዎች፣ ሰራተኞች፣ እና አገልግሎት አቅራቢዎች ጋር የቡድን ውይይት ለማድረግ ከጆርጅ ታውን የአየር ሁኔታ ማእከል ጋር አጋርነት ፈጥሯል፣ እና DOEE 500 ለሚሆኑ ኗሪዎች የጥናት ዳሰሳ አሰራጭቷል።

ከታች ያሉት የተነሱት ቁልፍ ጭብጦች ናቸው፥ 

  • ብዙ ሰዎች በጣም ከፍተኛ የሆነ ሙቀት በሚከሰትበት ወቅት በቤታቸው መቆየትን ይመርጣሉ።
  • የኋይል ከፍተኛ ወጪ ለአየር ማቀዝቀዣ መጠቀም የተለመደ ተግዳሮት ነው፣ እና በተለይ ተከራዮች ፈተናዎች ያጋጥሟቸዋል።
  • የተወሰኑ ኗሪዎች ስላሉ የማቀዝቀዣ መገልገያዎች እና ፕሮግራሞች አላወቁም። የትምህርት ተደራሽነት ለሁሉም ኗሪዎች እንዲደርስ በበርካታ ቋንቋዎች እና በተለያዩ ጣቢያዎች አማካኝነት ያስፈልጋል።
  • ደህንነት፣ ንጽህና፣ እና የጥገና ስጋቶች ኗሪዎች ነባር ፓርኮችን እና አረንጓዴ ቦታዎችን እንዳይጎበኙ ይከለክላቸዋል።
  • ብዙ ኗሪዎች በጎረቤታቸው ያሉ የተሻለ ጥላ ያላቸው ዛፎች እና አረንጓዴ ቦታዎች ላይ ፍላጎት ያሳያሉ።


ዲስትሪክቱ ለምንድነው እየሞቀ የመጣው?

በቅርብ ጊዜያት፣ የኮሎምቢያ ዲስትሪክት በከፊል በአየር ሁኔታ ለውጥ እና የከተማ ሙቀት የደሴት ውጤት ምክንያት የሚመጡ የሙቀት መጠን ለውጦች አጋጥሞታል። ለምሳሌ፣ የ በጣም ሞቃታማ ቀናት አማካይ ዓመታዊ ቁጥር ከ1985 ጀምሮ ጨምሯል እና ከ2009 ጀምሮ የማታ ጊዜ የሙቀት መጠን በፍጥነት ወደ ሞቃታማነት እየተቀየረ ነው። ከባለው ክፍለ-ዘመን ጋር ሲነጻጸር የበጋ ጊዜያት እየተራዘሙ ነው።  የሜሪላንድ እና የኮሎምቢያ ዲስትሪክት ስቴት አየር ሁኔታ የማጠቃለያ ሀሳቦች 2022 (ncics.org)  

የአየር ሁኔታ ለውጥ

የሰዎች ተግባር (የድንጋይ ከሰል ማቃጠል ዓይነት) የዓለም የሙቀት መጠንን እየጨመረ እና የአየር ሁኔታ ተፈጥሮዎችን ከታሪካዊ አዝማሚያዎቻቸው እየለወጠ እንደሆነ ሳይንትስቶች አሳይተዋል። በዲሲ ውስጥ የአየር ሁኔታ በምን መልክ ይለወጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ ለማየት ከታች ያለውን  የአየር ሁኔታ ማሰሻን  ይመልከቱ።  (ስለ የአየር ሁኔታ ማሰሻ የበለጠ ይማሩ። ) ተለዋዋጭ ሁኔታን፣ መዋቅሮችን፣ የልቀት ሁኔታ፣ እና የጊዜ መለኪያን መቀየር ይችላሉ።

የከተማ ሙቀት ደሴት

Conditions like those at the RFK Stadium parking lots contribute to the urban heat island effect.

በአየር ሁኔታ ለውጥ የሚጨምር የሙቀት መጠን በተጨማሪ፣ ዲስትሪክቱ የከተማ ሙቀት ደሴት (አርባን ሂት አይላንድ) (UHI) ተጽዕኖ ያጋጥመዋል። የ UHI ውጤት የፀሀይ ብርሃን በተነጠፉ ስፍራዎች እና ጣሪያዎች የሚሳብባቸው እና የሚያዝባቸው አካባቢዎች ውስጥ ይከሰታል። የተጨናነቁ የከተማ አካባቢዎች ውስጥ፣ ይህ የተሳበ/የተመጠጠ ሙቀት እንደ የአየር ማቀዝቀዣ እና መኪናዎች ዓይነት ካሉ ቴክኖሎጂዎች የሚለቀቅ ሙቀት ጋር ተጣምሮ ከአካባቢው የከተማ-ዙሪያ ወይም የገጠር አካባቢዎች የበለጠ በጉልህ ሞቃታማ የሆነ "ደሴትን" ይፈጥራል። የዛፎች እና አትክልቶች መኖር ከፀሀይ የሚመጣውን ጨረር በማዞር፣ ጥላ በመስጠት፣ እና እርጥበትን ወደ አትሞስፌር በመልቀቅ የሙቀት መጠንን አቀዝቅዞ ለማቆየት ሊረዳ ይችላል። አነስ ያሉ ዛፎች እና ከፍተኛ የማይበገሩ ስፍራዎች ብዛት (ወይም እንደ ንጣፍ፣ ህንጻዎች፣ እና መንገዶች ዓይነት ውሃን-የሚከላከሉ ስፍራዎች) ያላቸው ጎረቤቶች የበለጠ ሙቀትን ይስባሉ እና ይይዛሉ።


ተመጣጣኝ ያልሆነ የሙቀት ስጋት

ሙቀት በመላው ዲስትሪክት ተመጣጣኝ ባልሆነ ሁኔታ ይከሰታል። የተወሰኑ ጎረቤቶች ከሌሎች ይልቅ አነስ ያለ የዛፎች ቁጥር ወይም የበለጠ ንጣፍ አላቸው፣UHI በማምጣት፣ ይህ ደግሞ  የተወሰኑ ጎረቤቶች ከሌሎች ይልቅ 17° F ያህል የበለጠ እንዲሞቁ ያደርጋል! ዲስትሪክቱ በየት አካባቢ ለሙቀት የበለጠ እንደሚጋለጥ እና የበለጠ በሙቀት ተጠቂ የሆኑ ኗሪዎች የት እንደሚኖሩ በተሻለ ሁኔታ ለመረዳት፣ DOEE የሙቀት ተጋላጭነት እና ተጠቂነት ትንተና ሰርቷል። ከዚህ ትንተና የሚገኙ ውጤቶች ግብዓቶችን ዒላማ ለማድረግ እና የሙቀት ጣልቃ-መግቢያ ስትራቴጂዎችን ለማሳወቅ እና ቅድሚያ ለመስጠት ይረዳሉ።

ቀዝቃዛ የሆነ ሁኔታ ውስጥ ለመቆየት ምን ማድረግ እንደምችሉ

ግለሰቦች

በሙቀት ድንገተኛ ሁኔታ ወቅት እራስዎን እና ሌሎችን በደህንነት ለማቆየት እርምጃዎችን መውሰድ ይችላሉ። የሙቀት ድንገተኛ ሁኔታ ውስጥ የመጀመሪያ መሳሪያዎ እውቀት ነው፥ የድንገተኛ ሁኔታው ላይ በአካባቢ ሬዲዮ፣ ቴሌቪዥን እና ይፋዊ የማህበረሰብ ሚዲያ አካውንቶች አማካኝነት መረጃ እያገኙ ይቆዩ፣ እና ነጻ የሀገር ደህንነት እና ድንገተኛ ሁኔታ መቆጣጠሪያ ኤጀንሲ (HSEMA) መተግበሪያን ያውርዱ ወይም የሞባይል መሳሪያዎ ላይ ወቅታዊ መረጃን ለማግኘት  Alert DC  ይጠቀሙ።

በበጋው ወቅት፣ እራስዎን በደህንነት ለማቆየት የሚከተሉ ጠቃሚ-ምክሮችን ይውሰዱ፥

  • በማቀዝቀዣ ማእከል እረፍት ለመውሰድ ይሂዱ። የሙቀት መጠን ወይም የሙቀት ኢንዴክስ 95° F ሲደርስ ወይም ከዚያ በላይ ሲሆን የማቀዝቀዣ ማእከላትን ይከፍታል።
  • በጣም ከፍተኛ የሚሆንባቸው ሰዓታት ወቅት፣ 10:00 ጧት — 4:00 ከሰዓት፣ ወደ ውጭ ከመውጣት ይቆጠቡ።
  • ውጭ መሆን ካለብዎት፣ ጥላ ስር ይረፉ።
  • ብዙ ውሃ (ምን እንኳ ጥማት ባይኖርብዎትም!) ይጠጡ እና አልኮል ወይም ካፌይን ያላቸው መጠጦችን አይጠቀሙ።
  • ቀለል-ያለ ቀለም ያላቸው፣ ጠበቅ-የማይሉ ልብሶችን ይልበሱ።
  • እንዲያቀዘቅዝዎት፣ ቀዝቃዛ ሻወር ይውሰዱ።
  • ድብርት፣ ማቅለሽለሽ ከተሰማዎት፣ እና/ወይም የጡንቻ ህመም ከተሰማዎት፣ በፍጥነት የህክምና እርዳታ ይፈልጉ።

ሌሎችን በደህንነት ለማቆየት እንዲረዳ፣ የሚከተሉ እርምጃዎችን ለመውሰድ ያስቡ፥

  • በሙቀት የበለጠ ተጠቂ የሆኑ ጎረቤቶችን ይጠይቁ፣ እንደ አረጋውያን እና አካል ጉዳቶች ወይም ስር የሰደዱ ህመሞች ያሉባቸው ጎረቤቶች ዓይነትን።
  • ህጻናትን ወይም የቤት እንስሳትን በተሽከርካሪ ውስጥ በጭራሽ አይተው፣ መስኮቶች ትንሽ ተከፍተው እንኳ።
  • የሰውነት ድርቀት፣ የሙቀት ጭንቀት ምልክቶችን (ለምሳሌ፣ ከባድ ላብ፣ ድካም፣ ቁርጠቶች እና ብርድ ብርድ ማ )እና የሙቀት ስትሮክ ምልክቶችን (ለምሳሌ፣ ላብ የሌለው፣ ራስ-ምታት፣ ግራ መጋባት) ለመለየት ይማሩ፣ እና አጠገብዎ ያለው ሰው በሙቀት ሲቸገር ምን ማድረግ እንደሚችሉ ይወቁ።
  • በጎረቤትዎ ውስጥ ጥላ እንዲኖር መሞገት ወይም ጥላ ማቆም (ለምሳሌ፣ ዛፎች ወይም የጥላ ግንባታዎች)። ከታች ያለውን “የማቀዝቀዝ” ክፍል ይመልከቱ።

ድርጅቶች

የንግድ ተቋማት፣ ለትርፍ-የማይሰሩ ድርጅቶች፣ እና ሌሎች አሰሪዎች የማህበረሰብ አባላትን ከሙቀት ለመከላከል እንዲረዳ በርካታ እርምጃዎችን መውሰድ ይችላሉ።

  • በሥራ ቦታዎ ጥላ እንዲኖር ይሞግቱ ወይም ጥላ ያቁሙ
  • ኗሪዎች ከሙቀት እረፍት እንዲወስዱ ቦታ ለመስጠት ቦታዎን ይጠቀሙ።
  • በሥራ ላይ እያሉ ለሙቀት ሊጋለጡ ለሚችሉ ሰራተኞችዎ እንክብካቤ እና መገልገያዎችን ያቅርቡ፣ ጥላ መስጠት፣ ውሃ ማቅረብ፣ እና የቀኑ በጣም ሞቃታማ በሆኑ ሰዓታት ላይ የቤት ውጭ ስራ መቀነስ ዓይነትን።

ዲሲ'ን ቀዝቃዛ አድርጎ ማቆየት፥ ስልቶች

Keep Cool DC የኮሎምቢያ ዲስትሪክት የ በጣም ከፍተኛ ሙቀት ስጋቶችን ለመቆጣጠር እንዲችል ዘጠኝ አጠቃላይ ስልቶችን ያካትታል። እነዚህ ስልቶች ወደ ሁለት ክፍሎች ይቀናጃሉ፥ ማቀዝቀዝ እና በደህንነት መቆየት። ከእነዚህ ስልቶች የተወሰኑት ዲስትሪክቱ እርምጃ እንዲወስድ አዳዲስ እድሎችን ይለያሉ፣ እና የተወሰኑት ደግሞ ነባር የኤጀንሲ ተግባራትን ለማስፋፋት መንገዶችን ይለያሉ። ከስልቶቹ የተወሰኑት በአጭር-ጊዜ ውስጥ ሊፈጸሙ ይችላሉ፣ ሌሎች ግን ተፈጻሚ ለማድረግ ተጨማሪ ጊዜ ሊፈልጉ ይችላሉ። አንድ ላይ፣ እነዚህ ስልቶች ዲስትሪክቱ ለከፍተኛ ሙቀት እንዴት መዘጋጀት እና መቋቋም እንደሚችል ላይ መመሪያ ይሰጣሉ። 

እነዚህን ስልቶች ተግባራዊ ማድረግ ላይ በርካታ የዲስትሪክት ኤጀንሲዎች ይተባበራሉ፣ የሚከተሉትን ጨምሮ፥

  • የሀይል አጠቃቀም እና የአካባቢ ጥበቃ መምሪያ (DOEE)
  • የእርጅና እና የማህበረሰብ ኑሮ መምሪያ (DACL)
  • DC Health
  • የኮሎምቢያ ዲስትሪክት የመኖሪያ ቤት መስጫ ባለስልጣን (DCHA)
  • የኮሎምቢያ ዲስትሪክት የሕዝብ ቤተ-መጻህፍት (DCPL)
  • የኮሎምቢያ ዲስትሪክት የሕዝብ ትምህርት ቤት (DCPS)
  • የተጠቃሚ እና የቁጥጥር ጉዳዮች መምሪያ (DCRA)
  • የኮሎምቢያ ዲስትሪክት የስቴት አትሌቲክስ ማህበር (DCSAA)
  • የዲስትሪክት የትራንስፖርት መምሪያ (DDOT)
  • የጠቅላላ አገልግሎቶች መምሪያ (DGS)
  • የሰብዓዊ አገልግሎቶች መምሪያ (DHS)
  • ለእቅድ እና የኢኮኖሚ እድገት የምክትል ከንቲባ ቢሮ (DMPED)
  • የሥራ ቅጥር አገልግሎቶች መምሪያ (DOES)
  • የፓርክ እና የመዝናኛ መምሪያ (DPR)
  • የህዝብ ሥራዎች መምሪያ (DPW)
  • የጥቃቅን እና የአካባቢ የንግድ ሥራዎች እድገት መምሪያ (DSLBD)
  • የሀገር ደህንነት እና የድንገተኛ ሁኔታ ቁጥጥር ኤጀንሲ (HSEMA)
  • የሜትሮፖሊታን የፖሊስ መምሪያ (MPD)
  • የከተማ አስተዳዳሪ ቢሮ (OCA)
  • የቴክኖሎጂ ዋና ኦፊሰር ቢሮ (OCTO)
  • የአካል ጉዳተኝነት መብቶች ቢሮ (ODR)
  • የእቅድ ማውጫ ቢሮ (OP)
  • የሰዎች ምክር ቤት ቢሮ (OPC)
  • የስቴት ትምህርት የበላይ ተቆጣጣሪ ቢሮ (OSSE)
  • የተከራይ መብት ተሟጋች ቢሮ (OTA)
  • የኮሎምቢያ ዲስትሪክት የሕዝብ አገልግሎት ኮሚሽን (PSC)
  • የዋሽንግተን ሜትሮፖሊታን አካባቢ የትራንዚት ባለ-ስልጣን (WMATA)

ማቀዝቀዝ

ይህ ክፍል ዲስትሪክቱ የከተማ ሙቀትን ለመቀነስ የሚከተላቸውን ስልቶች ያብራራል። በ UHI ተጽዕኖ ምክንያት፣ የተወሰኑ ጎረቤቶች በህንጻዎች፣ መንገዶች፣ እና ሌሎች ጠንከር ያሉ ስፍራዎች ዛፎችን እና አረንጓዴ ቦታዎችን ስለሚተኩ የበለጠ ሙቀትን ይይዛሉ። ከፍተኛ ሙቀት የህዝብ ጤና ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል፣ ወሳኝ መሰረተ-ልማት እና መሳሪያዎችን ይጎዳል፣ የኋይል አጠቃቀም ዋጋን ከፍ ያደርጋል እና ኋይል የመቋረጥ ስጋትን ይጨምራል። ታስቦ በተሰራ እቅድ እና ዲዛይን፣ ዲስትሪክቱን ተመጣጣኝ በሆነ ሁኔታ ማቀዝቀዝ እንችላለን። ዛፎች የሙቀት መጠን ለመቀነስ ውጤታማ ናቸው፣ እና የፈጠራ ዲዛይኖች—እንደ አረንጓዴ ጣራዎች፣ ለኋይል ውጤታማ የሆኑ ህንጻዎች፣ አንጸባራቂ ስፍራዎች/ገጽታዎች፣ ጠፍጣፋ መንገዶች፣ እና አረንጓዴ መሰረተ-ልማት—ከተማችንን ቀዝቃዛ አድርጎ ለማቆየት መርዳት ይችላሉ።

ዲስትሪክቱን ቀዝቃዛ አድርጎ ለማቆየት፣ DOEE ቀጣይ ደረጃዎችን፣ እርምጃዎችን እና ሊቀርቡ የሚችሉ ነገሮችን ለመለየት የሚከተሉ ስልቶች ስር የተዘረዘሩ አጋር ኤጀንሲዎች ጋር በቅርበት ይሰራል።

በደህንነት መቆየት

ይህ ክፍል ዲስትሪክቱ በጣም በጣም ሞቃታማ ቀናት ላይ ኗሪዎችን እንዴት በደህንነት እንደሚያቆያቸው ያብራራል።  የአየር ሁኔታ ቀናትን ሞቃታማ፣ ማታዎችን የተወሰነ ሞቃታማ፣ እና የሙቀት ሞገዶችን ረዘም ያሉ እና የበለጠ ተደጋጋሚ እንዲሆኑ ያደርጋል። UHIን መጋፈጥ ስጋቶችን መቀነስ የሚችል ሲሆን፣ ዲስትሪክቱ አሁንም አደገኛ የሙቀት ክስተቶች ያጋጥሙታል። ለሙቀት በመዘጋጀት፣ የሙቀት መጨናነቅ እና የሙቀት ስትሮክ ምልክቶች ላይ ግንዛቤ በመፍጠር፣ እና ሁሉም ኗሪዎች በቀላሉ እፎይታ እንዲያገኙ በማረጋገጥ ህይወትን ማዳን እንችላለን።

ዲስትሪክቱ በከፍተኛ ሙቀት ወቅት በደህንነት እንዲቆይ ለመርዳት፣ DOEE ቀጣይ ደረጃዎችን፣ እርምጃዎችን እና ሊቀርቡ የሚችሉ ነገሮችን ለመለየት የሚከተሉ ስልቶች ስር የተዘረዘሩ አጋር ኤጀንሲዎች ጋር በቅርበት ይሰራል።

ወደ ፊት መሄድ

ለአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖዎች ምላሽ መስጠት በመላው የዲስትሪክት መንግስት ውስጥ ጥረቶችን ይጠይቃል። DOEE የዚህ እቅድ መተግበርን ያስተባብራል እና ቀጣይ እርምጃዎችን ለመለየት በእያንዳንዱ ስልት ስር ከተዘረዘሩ አጋር ኤጀንቶች ጋር ይሰራል። DOEE እና ሌሎች ኤጀንሲዎች በከፍተኛ ሙቀት የሚመጡ ፈተናዎችን ለመቋቋም በጣም ጥሩ መንገዶችን በተመለከተ ከባለ-ድርሻ አካላት እና የዲስትሪክት ኗሪዎች ጋር መስራታቸውን ይቀጥላሉ።

Copyright

District Department of Energy and Environment (DOEE)

Storymap

DOEE

Maps and Technical Assistance

The Cadmus Group

Conditions like those at the RFK Stadium parking lots contribute to the urban heat island effect.